ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
ምሳሌ 28:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕግን የማያከብሩ ሰዎች ክፉ ሰዎችን ያመሰግናሉ፤ ሕግን የሚያከብሩ ግን ክፉዎችን ይቃወማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፥ ሕግ ጠባቂዎች ግን ይቃወሟቸዋል። |
ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
በእነዚያም ቀኖች በይሁዳ በሰንበት ቀን ወይን የሚጨምቁ፥ እህልን፥ ወይን ጠጅን፥ የወይን ዘለላን፥ በለስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ በአህያ የሚጭኑ መሆናቸውን አየሁ፤ እነዚህንም ሁሉ በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኋቸው።
ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ ልጆች አንዱ ዮያዳዕ ነበር፤ ነገር ግን ከእርሱ ልጆች አንዱ የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነውን የሰንባላጥን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፤ ስለዚህም ዮያዳዕ ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲወጣ አደረግሁ።
ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።
ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?
ጳውሎስና በርናባስ ስለዚህ ጉዳይ ከሰዎቹ ጋር ንትርክና ክርክር አደረጉ፤ ከዚህ በኋላ ጳውሎስና በርናባስ በአንጾኪያ ካሉ ከሌሎች ጥቂት ወንድሞች ጋር ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄዱና ጉዳዩን ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች እንዲያቀርቡ ተወሰነ።
አንዳንዶች ግን እልኸኞች በመሆን የጌታን መንገድ በሕዝቡ ፊት እየተሳደቡ አናምንም ባሉ ጊዜ ከእነርሱ ራቀ፤ አማኞችንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ አዳራሽ በየቀኑ ያስተምር ነበር።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።
እናንተ እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ በነበርንበት ጊዜ መከራና ስድብ ደርሶብናል፤ ነገር ግን ታላቅ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ ወንጌሉን ለእናንተ እንድናስተምር አምላካችን ድፍረትን ሰጥቶናል።
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።