አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።
ምሳሌ 28:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለድኾች የሚሰጥ ከቶ አይቸገርም፤ ድኾችን ላለማየት ዐይኖቹን የጨፈነ ግን በሰዎች ዘንድ የተረገመ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤ አይቷቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፥ በድሆች ላይ ዐይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል። |
አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።
አቈይቶ በውድ ዋጋ ለመሸጥ እህሉን የሚያከማች ሰው፥ በሕዝብ ዘንድ የተረገመ ይሆናል፤ እህሉን ለገበያ የሚያቀርብ ሰው ግን፥ በሕዝብ ዘንድ የተመሰገነ ይሆናል።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር በምትኖርባቸው ከተሞች ሁሉ አንድ እስራኤላዊ ችግረኛ ሆኖ ቢገኝ የገዛ ወገንህ ስለ ሆነ አትጨክንበት፤ ገንዘብህንም አትንፈገው።