ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
ምሳሌ 26:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥላቻውን ቢሰውርም፥ የሚያደርገው ክፉ ነገር በሰው ሁሉ ዘንድ ግልጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተንኰሉ በሽንገላው ይሸፈን ይሆናል፤ ነገር ግን ክፋቱ በጉባኤ ይገለጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ፥ ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል። |
ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
ከዚህ በኋላ ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጦርነት በጀግንነት ብትዋጋ ታላቅዋን ልጄን ሜራብን እድርልሃለሁ፤” ሳኦል ይህን ያለበት ምክንያት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲሞት እንጂ እርሱ ዳዊትን ለመግደል ስላልፈለገ ነው።
በልቡም “ሜልኮልን ለዳዊት እሰጣለሁ፤ እርስዋም ዳዊትን እንድታጠምድልኝ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይገደላል” ሲል አሰበ። ስለዚህም ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን ጠርቶ “አሁን የእኔ ዐማች ትሆናለህ” አለው።