በመንገድ የሚተላለፉትን ሞኞች ወይስ ሰካራሞች ሁሉ የሚቀጥር አሠሪ ያገኘውን ሰው ሁሉ እንደሚያቈስል ቀስት ወርዋሪ ነው።
ሞኝን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።
ሞኝን ወይንም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር ሰው ነው፥ ሁሉን እንደሚያቆስል አዳኝ ነው።
ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ሳሉ የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ክፉዎችና ኃጢአተኞች ግን እጅግ የበረታ ቅጣትን ይቀበላሉ።
ሞኝነቱን ደጋግሞ የሚገልጥ ሞኝ ሰው ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው።
የሞኝ በምሳሌ መናገር ሰካራም በእጁ ላይ የተሰካውን እሾኽ ለማውጣት እንደ መታገል ያለ ነው።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደየሥራው ይሰጠዋል።