በአንተና በባልንጀራህ መካከል ክርክር ቢነሣ ከእርሱ ጋር ተወያይተህ አለመግባባትህን አስወግድ እንጂ የሌላን ሰው ምሥጢር አታውጣ።
ስለ ራስህ ጕዳይ ከባልንጀራህ ጋራ በምትከራከርበት ጊዜ፣ የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤
ሙግትህን ከባልንጀራህ ጋር በቀጥታ ፈጽም፥ የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥
ሐሜተኛ ሰው ምሥጢር አይጠብቅም፤ ታማኝ ሰው ግን ምሥጢርን ሰውሮ ይይዛል።
ሐሜተኛ ሰው ምሥጢር አይደብቅም፤ ስለዚህ በከንቱ ከሚለፈልፉ ሰዎች ራቅ።
አለበለዚያ ምሥጢር የማትጠብቅ መሆንክን የሚያውቅ ሰው ያዋርድሃል፤ ሊለወጥ የማይችልም መጥፎ ስም ይሰጥሃል።