ምሳሌ 25:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላዘነ ሰው መዝፈን፥ በብርድ ቀን ልብስ የማውለቅና በቊስል ላይ ሆምጣጤ የመጨመር ያኽል የከፋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላዘነ ልብ የሚዘምር፣ በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣ ወይም በሶዳ ላይ እንደ ተጨመረ ሖምጣጤ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዘነ ሰው ላይ የሚዘምር፥ በብርድ ቀን ልብስን እንደሚገፍና በቁስልም ላይ ሆምጣጤ እንደሚጨምር ሰው ነው። |
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?
እንዲህ ዐይነቱ በእምነት ላይ የተመሠረተ ጸሎት በሽተኛውን ያድነዋል፤ ጌታም ከበሽታው ይፈውሰዋል፤ የሠራው ኃጢአትም ቢኖር ይቅር ይባልለታል።