ምሳሌ 23:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበላኸውን እንኳ ትተፋዋለህ፤ እርሱን በማቈላመጥ የተናገርከውም ቃል ከንቱ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበላኸውን ትተፋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋለህ። |
ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።”