ምሳሌ 23:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባለ ሥልጣን ጋር ለመመገብ በአንድ ገበታ ላይ ብትቀርብ ማንነቱን አትዘንጋ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገዥ ጋራ ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣ በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባለ ሥልጣን ጋር ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ በፊትህ ያለውን በደኅና አስተውል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤ |
እነዚህ ሰዎች ያለ ኀፍረት በመዳራት በአንድነት ግብዣችሁ ላይ ሲገኙ እንቅፋት ይሆኑባችኋል፤ እነርሱ የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው፤ በነፋስ እንደሚገፋ፥ ዝናብ እንደሌለው ደመና ናቸው። በፍሬ ወራት እንኳ ፍሬ እንደማይገኝበት፥ ከስሩ እንደ ተነቀለና ሁለት ጊዜ እንደ ሞተ ዛፍ ናቸው።