ምሳሌ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማስተዋልን ጥራ፤ ለዕውቀትም ድምፅህን ከፍ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የመለየት ጥበብን ብትማጠን፣ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማስተዋልን ብትጣራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማመዛዘንን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብን ብትጠራት፥ ቃልህንም ለማስተዋል ብትሰጥ፥ ዕውቀትንም በታላቅ ቃል ብትፈልጋት፥ |
እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ የሚኖር አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!”
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።