La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ እርስዋ ቤት ብታመራ ጒዞህ ወደ ሞት ይሆናል፤ ወደ እርስዋ መሄድ ወደ ሙታን ዓለም እንደ መውረድ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤ መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፥ አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቤቷን በሞት አጠገብ አኖረች፥ አካሄድዋንም ከኀያላን ጋር ከምድር ወደ ሲኦል አቀናች።

Ver Capítulo



ምሳሌ 2:18
11 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።


ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ።


እርሱም ወደ ቤትዋ የሚሄዱ ሁሉ እንደሚሞቱና እስከ አሁንም ወደ ቤትዋ የገቡ ወደ ሙታን ዓለም ተሽቈልቊለው እንደወረዱ አያውቅም።


አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።


ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።