ሰው በሀብቱ ብዙ ወዳጆችን ያፈራል፤ ድኾችን ግን ያሉአቸው ጥቂት ወዳጆች እንኳ ይከዱአቸዋል።
ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።
ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፥ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።
ባለጠጋ ብዙ ወዳጆችን ይጨምራል፤ ድሃ ግን ያን ያለውን ያጣል።
ባለጸጋን ሀብቱ እንደ ምሽግ ሆኖ ይጠብቀዋል፤ ድኻውን ግን ድኽነቱ ያጠፋዋል።
ድኻ ሰው በጐረቤቱ ዘንድ እንኳ የተጠላ ነው። ሀብታሞች ግን ብዙ ወዳጆች አሉአቸው።
በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰት የሚናገር ከቅጣት አያመልጥም።