ምሳሌ 19:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላውን ሰው ለመበደል በሐሰት የሚመሰክር ሰው ካለ ፍትሕ ይጓደላል። ዐመፀኞችም ክፋት ማድረግ ያበዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናምንቴ ምስክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤ የክፉዎችም አፍ በደልን ይሰለቅጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወስላታ ምስክር በፍርድ ያፌዛል፥ የኀጥኣንም አፍ ክፋትን ይውጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአላዋቂ ልጅ የሚዋስ ፍርድን ያስነቅፋል፥ የኃጥኣንም አፍ ክፉ ቅጣትን ይውጣል። |
‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል’ ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያም በኋላ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”
ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።