ምሳሌ 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሜተኛ ሰው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሰኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ድረስ ይወርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል። |
በሕዝብህ መካከል እየዞርክ የስም አጥፊነት ወሬ አታሰራጭ፤ ሰውን ወደ ሞት አደጋ የሚያደርስ ምንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።