እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
ምሳሌ 18:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢት ጥፋትን ያመጣል፤ ትሕትና ግን ክብርን ያጐናጽፋል። ክብርን ግን ትሕትና ይቀድመዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
“የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።
ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።
ግብጽም ባዶዋን ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። “ ‘አንተ የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።
ገና መጸለይ ስትጀምር እግዚአብሔር ልመናህን ሰምቶአል፤ አንተ በእርሱ ዘንድ የተወደድክ ስለ ሆነ የጸሎትህን መልስ ልነግርህ መጥቼአለሁ፤ እንግዲህ የምነግርህን አዳምጠህ የራእዩን ትርጒም ተረዳ።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።