ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።
ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።
ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።
ትእዛዞችህን ከወርቅ ይልቅ አብልጬ እወዳለሁ፤ አዎ፥ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ አብልጬ እወዳለሁ።
ብር ወይም የተሰወረ ሀብት ለማግኘት ጥረት የምታደርገውን ያኽል ተግተህ ጥበብን ፈልጋት።
ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው የተባረከ ነው።
ስለዚህ ጥበብ ከብር ይበልጥ ትርፍ ትሰጣለች፤ ከወርቅም የተሻለ ጥቅም ታስገኛለች።
ጥበብንና ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ፤ እኔ የምልህን አትርሳ፤ ቸልም አትበለው።
ጥበብ ከሁሉ በላይ ስለ ሆነች እርስዋን ገንዘብ አድርግ፤ ያለህን ሁሉ ቢያስከፍልህም ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ።
ከእኔ የምታገኙት ጥቅም ዘላቂ ሀብትና ዕድገት የእኔ ናቸው። ከንጹሕ ወርቅና ከተነጠረ ብር የሚሻል ነው።
ጥበብ እንደ ገንዘብ ከለላ ነች፤ ከዚያም በላይ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትጠብቃለች።
ሰው የዓለሙን ሁሉ ሀብት ቢያገኝ፥ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ፥ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል?
“ለራሱ በምድር ላይ ሀብትን የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ፊት ግን ድኻ የሆነ ሰው እንዲሁ ይሆናል።”