ዮሴፍም “ይህ ያደረጋችኹት ነገር ምንድን ነው? እኔ ባለሁበት ደረጃ የሚገኝ ሰው በተለየ ጥበብ ሁሉን ነገር መርምሮ ማወቅ የማይችል መሰላችሁን?”
ምሳሌ 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ የሚፈርደው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ሥልጣን ነው፤ ስለዚህ ውሳኔዎቹ ዘወትር ትክክል ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ከንፈሮች እንደ አምላክ ቃል ይናገራሉ፤ አንደበቱ ፍትሕን ያዛባ ዘንድ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ብይን በንጉሥ አፍ ነው፥ አፉም በፍርድ አይስትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ በንጉሥ አፍ አለ፥ አፉም በፍርድ አይሳሳትም። |
ዮሴፍም “ይህ ያደረጋችኹት ነገር ምንድን ነው? እኔ ባለሁበት ደረጃ የሚገኝ ሰው በተለየ ጥበብ ሁሉን ነገር መርምሮ ማወቅ የማይችል መሰላችሁን?”
የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድን ነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ንገራቸው።”
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል።
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።