ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ አይታ በይቅርታ ታልፋለች።
ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።
ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።
ቍጣ ጥልን ያነሣሣል። ፍቅር ግን የማይጣሉትን ሁሉ ይሸፍናቸዋል።
ቊጣ ጭቅጭቅን ያነሣሣል፤ ትዕግሥት ግን ጠብን ያበርዳል።
ወንበዴ ክፉ ነገርን ያቅዳል ንግግሩም እንደ እሳት ያቃጥላል።
የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።
ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ግን ይበለጽጋል።
ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ግልፍተኛም ብዙ በደልን ይፈጽማል።
ወተት ቢናጥ ቅቤ ያስገኛል፤ የሰው አፍንጫ ቢጠመዘዝ ይደማል፤ ቊጣ ቢነሣሣ ጠብን ያመጣል።
በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በሰውነታችሁ ውስጥ ከሚዋጋው ከሥጋዊ ምኞታችሁ አይደለምን?
ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ፥ የኃጢአተኛውን ነፍስ ከሞት እንደሚያድንና የብዙ ኃጢአቱንም ይቅርታ እንደሚያስገኝለት ይወቅ።
ፍቅር ብዙ ኃጢአትን ስለሚሸፍን ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።