ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ፊልጵስዩስ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስፈልገኝንና ከሚያስፈልገኝም በላይ የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ፤ ይህም የእናንተ ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአብሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያስፈልገኝን ሁሉ፣ ከሚያስፈልገኝም በላይ ተቀብያለሁ፤ የላካችሁትንም ስጦታ ከአፍሮዲጡ እጅ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ፤ ይህም መዐዛው የጣፈጠ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቼአለሁ። |
ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ስለ ስእለት መፈጸም ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በበጎ ፈቃድ ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በተለመዱት የሃይማኖት በዓላት ላይ ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደዚህ ያለውም የምግብ ቊርባን መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤
ትኲር ብሎ ወደ መልአኩ ተመለከተና በመደንገጥ “ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?” አለ። መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ለድኾች የምታደርገው ምጽዋት መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል፤
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ይህ የምትፈጽሙት የልግሥና አገልግሎት የክርስቲያኖችን ችግር ከማስወገዱም በላይ ሰዎች ለእግዚአብሔር ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋቸዋል።
ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
ስለዚህ ማግኘትንም ሆነ ማጣትን ዐውቃለሁ፤ በማንኛውም ቦታ ሆነ በየትኛውም ጊዜ የመጥገብንና የመራብን፥ የማግኘትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።