ዘኍል 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መባቸውን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያቀረቡአቸውም መባዎች በየሁለቱ አለቆች ስም አንድ ሠረገላ፥ እንዲሁም በእያንዳንዱ አለቃ ስም አንድ በሬ ሆኖ፥ ስድስት ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ነበሩ፤ እነዚህንም መባዎች በመገናኛው ድንኳን ፊት አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት የተሸፈኑ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ይኸውም ከእያንዳንዱ አለቃ አንዳንድ በሬ እንዲሁም ከየሁለቱ አለቆች አንድ ሠረገላ ስጦታ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መባቸውንም በጌታ ፊት አመጡ፥ የተሸፈኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ ለሁለትም አለቆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሠረገላ ለእያንዳንዱም አለቃ አንዳንድ በሬ አመጡ፤ በማደሪያው ፊት አቀረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፤ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፤ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በድንኳኑ ፊት አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፥ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች አሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፥ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በማደሪያው ፊት አቀረቡ። |
እነዚህም ምርኮኞች ተመልሰው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎች ቀድሞ በነበረበት ቦታ ቤተ መቅደሱን እንደገና መልሶ ለመሥራት ይረዳ ዘንድ በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ የመባ ስጦታ አበረከቱ።
ወንድሞቻችሁን ሁሉ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቅዱስ ተራራዬ በፈረሶች፥ በሠረገሎች፥ በጋሪዎች፥ በበቅሎዎችና በግመሎች አድርገው ከተለያዩ አገሮች ለእግዚአብሔር እንደ መባ ያመጡአቸዋል፤ እነርሱንም የሚያመጡአቸው እስራኤላውያን የእህል ቊርባንን በሥርዓት በነጻ ዕቃ ለእኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ አድርገው ነው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።