አውራውን በግ የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀርበዋል፤ እርሱንም በመሶብ ካለው እንጀራ ጋር ያቀርበዋል፤ ቀጥሎም የእህሉን ቊርባንና የመጠጡን መባ ያቀርባል።
ዘኍል 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን በር መግቢያ ላይ ናዝራዊው ጠጒሩን ላጭቶ የአንድነት መሥዋዕት በሚቃጠልበት እሳት ላይ ያኖረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከዚያም ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጨው፤ ጠጕሩንም ወስዶ ከኅብረቱ መሥዋዕት ሥር በሚነድደው እሳት ውስጥ ይጨምረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዝራዊውም የተቀደሰውን የራሱን ጠጉር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጫል፥ የተቀደሰውንም ራስ ጠጉር ወስዶ ከአንድነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሳለውም የተሳለውን የራስ ጠጕር በምስክሩ ድንኳን አጠገብ ይላጫል፤ የስእለቱንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደኅንነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዝራዊውም የተለየውን የራሱን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ይላጫል፥ የመለየቱንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደኅንነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። |
አውራውን በግ የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀርበዋል፤ እርሱንም በመሶብ ካለው እንጀራ ጋር ያቀርበዋል፤ ቀጥሎም የእህሉን ቊርባንና የመጠጡን መባ ያቀርባል።
“ስእለት ተስሎ በናዝራዊነት እስካለ ድረስ ራሱን ምላጭ አይንካው፤ የናዝራዊነት ጊዜው እስኪፈጸም ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ይሆናል፤ የራሱንም ጠጒር ያሳድጋል።
ጳውሎስ ከወንድሞች ጋር ብዙ ቀኖች በቆሮንቶስ ከቈየ በኋላ ተሰናብቶአቸው ወደ ሶርያ ሄደ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ነገር ግን ስለት ስለ ነበረበት ከመሄዱ በፊት ክንክሪያ በሚባል ቦታ ራሱን ተላጨ።
እነርሱን ውሰድና ከእነርሱ ጋር ሆነህ ራስህን አንጻ፤ ጠጒራቸውንም እንዲላጩ ለቤተ መቅደስ የሚሰጠውን የመባ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ይህን ብታደርግ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና አንተም ራስህ ለሕግ ታዛዥ መሆንክህን ሁሉም ያውቃሉ።
ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ሰዎቹን ወሰደና በማግስቱ ከእነርሱ ጋር ራሱን አነጻ፤ የሚነጹባቸው ቀኖች መቼ እንደሚሆንና ስለ እያንዳንዱም የሚሰጠው የመባ ገንዘብ የሚከፈልበት ጊዜ መቼ እንደሚሆን ለማስታወቅ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።