ዘኍል 4:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ መሸከም ያለባቸው ተራዳዎችን፥ መወርወሪያዎችን፥ ምሰሶችን፥ የማደሪያው ድንኳን የሚቆምባቸውን እግሮች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቶቻቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ተግባራቸው ይህ ነው፤ የማደሪያውን ሳንቃዎች፣ መወርወሪያዎች፣ ምሰሶዎችንና መቆሚያ እግሮቻቸውን፣ ይሸከማሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ የሚሸከሙት፥ የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶዎቹንም፥ እግሮቹንም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ፥ የድንኳኑ ሳንቆች፥ መወርወሪያዎቹም፥ ተራዳዎቹም፥ እግሮቹም፥ መሸፈኛዎቹም፥ መቀመጫዎቹም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ፥ የማደሪያው ሳንቆች፥ መወርወሪያዎቹም፥ ተራዳዎቹም፥ እግሮቹም፥ |
እንዲሁም በድንኳኑ ዙሪያ የሚገኘውን አደባባይ ምሰሶችን፥ እግሮቻቸውን፥ ካስማዎችን፥ አውታሮችንና ለእነዚህ ሁሉ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ነው፤ እያንዳንዱም መሸከም ያለበትን ዕቃ በየስሙ ትመድብለታለህ።