ነገር ግን እኛ አገልጋዮችህ ለጦርነት የታጠቅን ሁሉ በእግዚአብሔር መሪነት ለመዋጋት ልክ አንተ ጌታችን እንደምታዘን ወደ ማዶ እንሻገራለን።”
ዘኍል 32:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሙሴ ስለ እነርሱ ለካህኑ ለአልዓዛር፥ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች ሁሉ ይህን ትእዛዝ አስተላለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ ለካህኑ ለአልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ነገድ ቤተ ሰብ አለቆች እነርሱን አስመልክቶ ትእዛዝ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን የነዌንም ልጅ ኢያሱን የእስራኤልንም ልጆች ነገድ አለቆች ስለ እነርሱ አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን፥ የነዌንም ልጅ ኢያሱን፥ የእስራኤልንም ነገድ አባቶች አለቆች አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን የነዌንም ልጅ ኢያሱን የእስራኤልንም ልጆች ነገድ አለቆች ስለ እነርሱ አዘዘ። |
ነገር ግን እኛ አገልጋዮችህ ለጦርነት የታጠቅን ሁሉ በእግዚአብሔር መሪነት ለመዋጋት ልክ አንተ ጌታችን እንደምታዘን ወደ ማዶ እንሻገራለን።”
“የጋድና የሮቤል ሰዎች ዮርዳኖስን ተሻግረው በእግዚአብሔር መሪነት ለጦርነት የሚዘጋጁ ከሆነና በእነርሱም ርዳታ ምድሪቱን የምትወርሱ ከሆነ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርጋችሁ ስጡአቸው።