ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህ የተናገራችሁት ሁሉ እውነት ከሆነ እዚህ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ጦርነት ለመሄድ ተዘጋጁ።
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ብታደርጉ ማለትም በእግዚአብሔር ፊት ታጥቃችሁ ለጦርነት ብትዘጋጁ፣
ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህንስ ነገር ብታደርጉ፥ ተዘጋጅታችሁም በጌታ ፊት ወደ ጦርነት ብትሄዱ፥
ሙሴም አላቸው፥ “ይህንስ እንዳላችሁት ብታደርጉ፥ ታጥቃችሁም በእግዚአብሔር ፊት ወደ ጦርነት ብትሄዱ፥
ሙሴም አላቸው፦ ይህንስ ነገር ብታደርጉ፥ ተዘጋጅታችሁም በእግዚአብሔር ፊት ወደ ሰልፍ ብትሄዱ፥
የጦር ሰዎቻችሁ ሁሉ ዮርዳኖስን መሻገር፥ በእግዚአብሔር አዛዥነት በጠላቶቻችን ላይ መዝመት፥ እግዚአብሔር ድል አድርጎ፥ ምድራቸውን እስኪወስድ ድረስ መዋጋት አለባቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለው ምድር የእናንተ ርስት መሆኑን እግዚአብሔር ያረጋግጥላችኋል።
ኢያሱ የሮቤልንና የጋድን ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤
ከዚህ በኋላ ኢያሱ የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ ያሉትን የምናሴን ነገዶች በአንድነት ጠርቶ፥
የሮቤል፥ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር በሚገኘው በሴሎ ካሉት ከእስራኤላውያን ዘንድ ተነሥተው በሙሴ አማካይነት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተሰጣቸው ምድር ወደ ገለዓድ ተመለሱ።