La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በለዓምም በማግስቱ ጠዋት ሲነጋ ተነሥቶ፥ ለባላቅ ሹማምንት “እንግዲህ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ እኔ ከእናንተ ጋር እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛል” አላቸው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማግስቱም ጧት በለዓም ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፣ “ዐብሬአችሁ እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛልና እናንተ ወደ አገራችሁ ተመለሱ አላቸው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን ሹማምንት፦ “ከእናንተ ጋር እንድሄድ ጌታ አልፈቀደምና ወደ ምድራችሁ ሂዱ” አላቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነ​ሥቶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ል​ኝ​ምና ወደ ጌታ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፦ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደምና ወደ ምድራችሁ ሂዱ አላቸው።

Ver Capítulo



ዘኍል 22:13
3 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም በለዓምን “ከነዚህ ሰዎች ጋር አትሂድ፤ የተባረኩ ስለ ሆነ የእስራኤልን ሕዝብ አትርገም” አለው።


ስለዚህ የሞአብ ሹማምንት ወደ ባላቅ ተመለሱና በለዓም አብሮአቸው ለመምጣት እምቢ እንዳለ ነገሩት።


ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር አንተን ስለሚወድህ መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው። እግዚአብሔር እናንተን ይወዳችኋል።