ዘኍል 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የምናሴ ልጆች ይሆናሉ፤ የምናሴ ነገድ መሪ የጴዳጹር ልጅ ገማልኤል ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህም የምናሴ ነገድ ይቀጥላል፣ የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ነበረ፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ይሆናል፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፈዳሱር ልጅ ገማልያል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ይሆናል፤ የምናሴም ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበረ። |