አሮንና ልጆቹ ዘወትር ወደ ድንኳን ሲገቡ ወይም በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ ይለብሱታል፥ በዚህ ዐይነት የውስጥ ሰውነታቸው ስለማይጋለጥ ከሞት ይድናሉ፤ ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር ሥርዓት ነው።
ዘኍል 18:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርጥ የሆነውን ነገር ለእግዚአብሔር ካቀረባችሁ በኋላ በምትመገቡበት ጊዜ በደል አይኖርባችሁም፤ ነገር ግን ምርጥ የሆነው ነገር ከእርሱ ላይ ሳይነሣ ከስጦታው በመመገብ የእስራኤላውያንን የተቀደሰ ስጦታ እንዳታስነውሩ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተመረጠውን ክፍል ካቀረባችሁ በዚህ በደለኞች አትሆኑም፤ ደግሞም የተቀደሰውን የእስራኤላውያንን መባ አታረክሱም፤ አትሞቱምም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢአት አይሆንባችሁም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታርክሱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታረክሱም። |
አሮንና ልጆቹ ዘወትር ወደ ድንኳን ሲገቡ ወይም በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ ይለብሱታል፥ በዚህ ዐይነት የውስጥ ሰውነታቸው ስለማይጋለጥ ከሞት ይድናሉ፤ ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር ሥርዓት ነው።
“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፦ የተቀደሰ ስሜን እንዳታረክሱ የእስራኤል ልጆች ለይተው ለእኔ የሚያቀርቡትን መባ ሁሉ በአክብሮት ተቀብላችሁ በቅድስና ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የረከሰ ምግብ በመሠዊያዬ ላይ እያኖራችሁ ‘መሠዊያህን ያረከስነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ያረከሳችሁትማ ገበታዬ በዚህ በእናንተ ነገር ይናቃል ብላችሁ ስላሰባችሁ ነው።
እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤