ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።
ዘኍል 18:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ የሚገኘውም ሥጋ በመወዝወዝ ልዩ መባ ሆኖ እንደሚቀርበው እንደ ፍርምባውና እንደ ቀኙ ወርች ለእናንተ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚወዘወዘው ቍርባን ፍርምባና የቀኙ ወርች የአንተ እንደ ሆነ ሁሉ የእነዚህም ሥጋ የአንተ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚወዘወዘው ፍርምባና የቀኙ ወርች ለአንተ እንደሆነ እንዲሁ ሥጋቸው ለአንተ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋውም ለአንተ ይሆናል፤ እንደሚያቀርቡት ፍርምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአንተ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋቸውም ለአንተ ይሆናል፤ እንደ መወዝወዝ ፍርምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአንተ ይሆናል። |
ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።
ስለዚህም የወጥቤቱ ሠራተኛ ምርጥ የሆነውን የታናሽ ብልት ሥጋ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን “ተመልከት፤ ይህ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ምርጥ ሥጋ ነው፤ እኔ ከጋበዝኳቸው እንግዶች ጋር ሆነህ እንድትበላ ያስቀመጡልህ ስለ ሆነ እርሱን ተመገብ” አለው። ስለዚህም በዚያ ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር አብሮ ተመገበ፤