በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
ዘኍል 15:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመጠጥ ቍርባንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሦስተኛ እጅ ወይን ታቀርባለህ። |
በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር አንድ ኪሎ ግራም ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ከአንድ ሊትር ተጨምቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት ጋር ለውሰህ አቅርብ፤ አንድ ሊትር የወይን ጠጅም መባ አድርገህ አፍስስበት።
ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።