ዘኍል 15:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በልብሶቻችሁም ጫፍ ላይ የሚታዩት ዘርፎች ትእዛዞቼን ሁሉ እንድትፈጽሙ ያስታውሱአችኋል፤ እናንተም በፍጹም ለእኔ የተገዛችሁ ትሆናላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ትእዛዞቼን ሁሉ ለመፈጸም ታስባላችሁ፤ ለአምላካችሁም የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ትእዛዜን ሁሉ አስታውሱት አድርጉትም፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዙን ታስቡና ታደርጉ ዘንድ፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዜን ሁሉ ታስቡና ታደርጉ ዘንድ፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ ዘርፉ በልብሳችሁ ላይ እንዲታይ ይሁን። |
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።