በታላላቅና በታናናሽ በዓላት ቀኖች ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር የሚቀርበው የኽህል መባ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ለእግዚአብሔር የሚሰግደው ሰው ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የፈቀደውን ያኽል ያቅርብ። ከእያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ መባ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።
ዘኍል 15:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
በታላላቅና በታናናሽ በዓላት ቀኖች ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር የሚቀርበው የኽህል መባ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ለእግዚአብሔር የሚሰግደው ሰው ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የፈቀደውን ያኽል ያቅርብ። ከእያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ መባ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።
ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።