ዘኍል 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መለከቶቹን የሚነፉት ካህናቱ የአሮን ልጆች ይሆናሉ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የሚተላለፍ ቋሚ ሥርዓት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መለከቶቹን ካህናቱ የአሮን ልጆች ይንፉ፤ ይህም ለእናንተና ለሚመጡት ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቶቹን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሁንላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቶቹን ይንፉ፤ እነርሱም ለልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሁኑ። |
ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር።