ዘኍል 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ከግብጽ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ከምስክሩ ድንኳን በላይ የረበበው ደመና ተነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ዓመት፣ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ድንኳን ላይ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። |
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦
ዘግይተው ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እንዲያከብሩ ተፈቅዶላቸዋል፤ ሲያከብሩም እርሾ የሌለበትን ቂጣ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ።
እነርሱም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን በምሽት በሲና ምድረ በዳ በዓሉን አከበሩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።