ከዚህ በኋላ ዳርዮስ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ ለሆንከው ለታተናይ፥ ለሸታርቦዝናይና በኤፍራጥስ ምዕራብ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችሁ ሁሉ፦ ከቤተ መቅደሱ ራቁ፤
ነህምያ 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ አልሁት፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በደኅና እንዲያሳልፉኝ ከኤፍራጥስ ማዶ ላሉት አገረ ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ መልካም ፈቃዱ ቢሆን፥ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ እንዲያሳልፉኝ ከወንዙ ማዶ ላሉት ገዢዎች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብዳቤ ይስጠኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ አገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት አገረ-ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ |
ከዚህ በኋላ ዳርዮስ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ ለሆንከው ለታተናይ፥ ለሸታርቦዝናይና በኤፍራጥስ ምዕራብ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችሁ ሁሉ፦ ከቤተ መቅደሱ ራቁ፤
“እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከኤፍራጥስ ምዕራብ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ በሰማይ አምላክ ሕግ ምሁር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ ትሰጡት ዘንድ አዝዣለሁ።
ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር።
ንጉሠ ነገሥቱ የሰጣቸውንም ሰነድ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ላሉት ገዢዎችና ባለሥልጣኖች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ በማገዝ ድጋፋቸውን ሰጡ።
ንጉሠ ነገሥቱም ጥቂት የጦር መኰንኖችና ፈረሰኞች ከእኔ ጋር እንዲሄዱ አደረገ፤ እኔም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ወደሚገኘው ክፍለ ሀገር ጒዞዬን ቀጠልኩ፤ እዚያ እንደ ደረስኩም ደብዳቤዎቹን ለአገረ ገዢዎቹ አስረከብኩ፤
የገባዖን ተወላጅ የሆነው መላጥያ፥ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ያዶንና የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች የኤፍራጥስ ምዕራብ አገረ ገዢ እስከሚኖርበት ቤት ድረስ ያለውን ክፍል ሠሩ።