ናሆም 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሦራውያን በእናንተ ላይ የጫኑትን የጭቈና አገዛዝ አስወግዳለሁ፤ እናንተን ያሰሩበትንም እግር ብረት እሰብራለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ቀንበራቸውን ከዐንገትህ ላይ አንሥቼ እሰብራለሁ፤ የታሰርህበትንም ሰንሰለት በጥሼ እጥላለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ቀንበሩን ከአንቺ እሰብራለሁ፥ እስራትሽንም እበጥሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ቀንበሩን ከአንተ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ። |
በዚያንም ጊዜ እናንተን ከአሦራውያን የጭቈና አገዛዝ ነጻ አወጣችኋለሁ፤ ከዚያን በኋላ የአገዛዝ ቀንበራቸው ከውፍረታችሁ የተነሣ ይሰበራል እንጂ በእናንተ ጫንቃ ላይ እንደተጫነ አይቀርም።”
አሦራውያንን ለእስራኤል በሰጠኋት ምድሬ ላይ እደመስሳቸዋለሁ፤ በተራሮቼም ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ከአሦራውያን የአገዛዝ ቀንበርና ከነበረባቸውም ከባድ ሸክም ነጻ አወጣቸዋለሁ።
በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! ከብዙ ጊዜ በፊት ለኔ መታዘዝና እኔን ማገልገል ትተሻል፤ በእርግጥም በተራራው ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር ሌሎች አማልክትን በማምለክ አመንዝረሻል።
እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል።
በባርነት እንዳትገዙ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ተጭኖአችሁ የነበረውን የባርነት ቀንበር ሰብሬ፥ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአለሁ።”