እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
ማቴዎስ 9:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ! ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም!” አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዞር በሉ፤ ብላቴናዪቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው፤ እነርሱ ግን ሣቁበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ዞር በሉ፤” አላቸው። እነርሱ ግን ሳቁበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት። |
እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።
ሰዎቹም በማፌዝ ሳቁበት፤ ኢየሱስ ግን ሁሉንም ከቤት አስወጣ፤ የልጅትዋን አባትና እናት ከእርሱም ጋር የነበሩትን አስከትሎ፦ ልጅትዋ ወደነበረችበት ክፍል ገባ።
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
ጴጥሮስ ግን ሁሉንም ወደ ውጪ አስወጣና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ አስከሬኑም መለስ አለና “ጣቢታ! ተነሺ!” አለ፤ እርስዋም ዐይኖችዋን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም አየች፤ ተነሥታም ቁጭ አለች።