ማቴዎስ 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገችው “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ በልብዋ አስባ ስለ ነበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በልቧ፣ “የልብሱን ጫፍ እንኳ ብነካ እፈወሳለሁ” ብላ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልብዋ “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ፤” ብላ ታስብ ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልብዋ “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ትል ነበረችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልብዋ፦ ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና። |
በዚህም ምክንያት የጳውሎስን አካል የነካውን ልብስና መሐረብ እየወሰዱ በሽተኞቹን ሲያስነኩአቸው ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡላቸው ነበር።