ማቴዎስ 6:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ ከንቱ ቃል በመደጋገም አትለፍልፉ፤ እነርሱ በመደጋገማቸው ብዛት እግዚአብሔር ጸሎታቸውን የሚሰማቸው ይመስላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። |
እነርሱንም አልሰማም ቢል ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም የማይሰማ ከሆነ እንደ አረመኔና ተጸጽቶ እንደማይመለስ ኃጢአተኛ ቊጠረው።
ከእነርሱ ጥቂት ራቅ ብሎ ሄደና፥ በመሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ፥ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “አባት ሆይ! የሚቻል ከሆነ ይህ የመከራ ጽዋ ከእኔ ወዲያ ይለፍ! ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”
እንደገናም ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ርቆ ሄደና “አባቴ ሆይ! ይህ የመከራ ጽዋ ሳልጠጣው ሊያልፍ የማይቻል ከሆነ የአንተ ፈቃድ ይሁን” ሲል ጸለየ።
ነገር ግን እስክንድር አይሁዳዊ መሆኑን ሰዎቹ ሁሉ ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤሚስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያኽል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮኹ።