በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር በምትገኝ በቤተልሔም ከተማ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ማቴዎስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም ከመላው የይሁዳ ምድር፥ ከዮርዳኖስም ዙሪያ ሁሉ፥ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም፥ ከይሁዳ ሁሉና በዮርዳኖስም ዙሪያ ካሉ አውራጃዎች ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ |
በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር በምትገኝ በቤተልሔም ከተማ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ከይሁዳ ምድርና ከኢየሩሳሌም ከተማ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፤ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ይጠመቁ ነበር።
ኢየሱስ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “የሕግና የነቢያት መጻሕፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቈይተው ነበር፤ ከዚያም ወዲህ የሚነገረው የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ቃል ነው፤ እያንዳንዱም ሰው ወደዚያች መንግሥት ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋል።
ስለዚህ ዮሐንስ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ባሉት አገሮች ሁሉ እየተዘዋወረ፦ “ለኃጢአታችሁ ይቅርታ እንድታገኙ ንስሓ ገብታችሁ ተጠመቁ፤” እያለ ያስተምር ነበር።
ሊጠመቁ ወደ እርሱ የመጡትን ብዙ ሕዝብ ዮሐንስ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የመርዘኛ እባብ ልጆች! ከሚመጣው ከእግዚአብሔር ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?