ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ማቴዎስ 27:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጠገቡ ያልፉ የነበሩትም ሰዎች በንቀት ራሳቸውን እየነቀነቁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ ይሉት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፦ |
ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር።
ስድብ ልቤን ስለ ሰበረው ተስፋ ቈረጥኩ፤ የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልተገኘም።
እግዚአብሔር ጽኑ ቊጣውን በእኛ ላይ ባወረደበት ቀን በእኛ ላይ እንደ ደረሰው ያለ መከራ የደረሰበት ሰው ያለ እንደ ሆነ እናንተ አላፊ አግዳሚዎች እስቲ እዩ ተመልከቱ! ይህ ሁኔታ ለእናንተ ቀላል ነውን?