ማቴዎስ 25:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኋላም የቀሩት ልጃገረዶች መጡና፦ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዘግየት ብለው ሌሎቹ ልጃገረዶች መጥተው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የቀሩቱ ደናግል መጥተው ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን፤’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቍኦነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። |
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።