ማቴዎስ 23:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱንም ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፣ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ግን ይከበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱንም ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ከፍ ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። |
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
ጽድቅን አግኝቶ ወደ ቤቱ የተመለሰው ይህ ቀራጭ ነው እንጂ ፈሪሳዊው አይደለም እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።