ማቴዎስ 21:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይኑ አትክልት ባለቤት እንደገና ቊጥራቸው ከፊተኞቹ የሚበልጥ ሌሎችን አገልጋዮች ደግሞ ላከ። ገበሬዎቹ በእነርሱም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ከፊተኞቹ የሚበልጡ ሌሎች ባሮቹን ላከ፤ ገበሬዎቹም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ከፊተኞቹ የሚበዙ ሌሎች ባርያዎችን ላከ፤ እነርሱንም እንዲሁ አደረጉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፤ እንዲሁም አደረጉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፥ እንዲሁም አደረጉባቸው። |
“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።