ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤
ማቴዎስ 21:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ሁሉ አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ በመገለባበጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን ወንበሮች ገለበጠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦ |
ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤
“የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።
“ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”
እንዲሁም ችሎታው በሚፈቅድለት መጠን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያመጣል፤
“አንድ ሰው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ማቅረብ ባይችል፥ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ስለ ኃጢአቱ ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት እንጂ የእህል መባ ስላልሆነ የወይራ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት።
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።
ኢየሱስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያውም ያለውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም መሽቶ ስለ ነበር ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ።