ማቴዎስ 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አንድ ሰዓት ገደማም ወጥቶ ሌሎች ሰዎች ቆመው አገኘና ‘እናንተስ ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው?’ ሲል ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰዓት በኋላም በዐሥራ አንድ ሰዓት ገደማ ወጥቶ ቆመው የነበሩ ሌሎች ሰዎች አገኘና፣ ‘ቀኑን ሙሉ ያለ ሥራ እዚህ ለምን ትቆማላችሁ?’ በማለት ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዐሥራ አንድ ሰዓት ገደማም ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና ‘ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ ለምን ትቆማላችሁ?’ አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና ‘ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ?’ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና፦ ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው። |
የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነው፤ እርስዋና መንደሮችዋ ኲራት ተሰምቶአቸው ነበር። የተትረፈረፈ ምግብና የተዝናና ኑሮ ቢኖራቸውም ችግረኞችንና ድኾችን አይረዱም ነበር።
ይህን ያሉት የአቴና ነዋሪዎችና በአቴና የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች ሁሉ አዲስ ነገር በመናገርና በመስማት ብቻ ጊዜያቸውን ማሳለፍ ይወዱ ስለ ነበር ነው።