እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
ማቴዎስ 20:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለእያንዳንዱ በቀን አንድ ዲናር ሊከፍል ተዋውሎ፥ ሠራተኞችን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከተስማሙ በኋላ ሠራተኞቹን በወይኑ ቦታ አሰማራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሠራተኞቹ ጋር በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ቦታ ሰደዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው። |
እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
ኢዮስያስ በነገሠ በስምንተኛ ዓመቱ፥ ገና ወጣት ሳለ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን አምላክ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመረ፤ ከአራት ዓመት በኋላም የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችን ጣዖቶች ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ማስወገድ ጀመረ፤
“ነገር ግን ያ አገልጋይ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ሳለ መቶ ዲናር ያበደረውን የሥራ ጓደኛውን አገኘና አንገቱን አንቆ ይዞ፥ ‘ያበደርኩህን ገንዘብ ክፈለኝ!’ አለው።
የወይኑ አትክልት ባለቤትም ከሠራተኞቹ ለአንዱ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ወዳጄ ሆይ! ምንም አልበደልኩህም፤ የተዋዋልነው በቀን አንድ ዲናር ልከፍልህ አይደለምን?
እርሱ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ሌላም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገና በእናቱ ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል።
በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዳ ማደሪያው ባለቤት ሰጠና ‘ይህን ሰው በጥንቃቄ አስታምልኝ፤ ተጨማሪ ወጪ ብታደርግም በምመለስበት ጊዜ እከፍልሃለሁ፤’ አለው።
“እስቲ ገንዘቡን አሳዩኝ፤ በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው” አሉት።
ከአራቱ እንስሶች መካከል የመጣ የሚመስል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህ ድምፅ “ግማሽ ኪሎ ያኽል ስንዴ የአንድ ቀን ደመወዝ፥ ለአንድ ኪሎ ተኩል ያኽል ገብስ ለአንድ ቀን ደመወዝ ይሁን፤ ዘይትንና ወይንን ግን አትጒዳ!” ሲል ሰማሁ።
ሳሙኤል ግን ገና በልጅነቱ ከበፍታ የተሠራ ሸሚዝ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር፤ ይህም ቃል በዕብራይስጡ ካህኑ ለሚለብሰው ልብስ ወይም በደረቱ ላይ ስለሚያደርገው ነገር መጠሪያ ነው።
ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።