በዚህም ዐይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዐይነት ይገኛል።
ማቴዎስ 15:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ ወርዶ ወደ ውጪ እንደሚወጣ አታስተውሉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ ዘልቆ፣ ከዚያም ወደ ውጭ እንደሚወጣ አታውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አፍ የሚገባው ሁሉ ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ እንደሚወጣ አታስተውሉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? |
በዚህም ዐይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዐይነት ይገኛል።
ስለዚህ ደግ ሰው ከመልካም ልቡ መልካምን ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከመጥፎ ልቡ ክፉውን ነገር ያወጣል። ሰው በአፉ የሚናገረው ከልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።
“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።