ማቴዎስ 15:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተም እስከ አሁን ገና የማታስተውሉ ናችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተም እስካሁን አይገባችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እናንተም እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም እንዲህ አለ “እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? |
ገና የማታስተውሉ ናችሁን? አምስት እንጀራ ለአምስት ሺህ ሰው እንደበቃና የተረፈውን ፍርፋሪ ምን ያኽል መሶብ ሙሉ እንዳነሣችሁ አታስታውሱምን?
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተም ደግሞ ይህን አታስተውሉምን? ከውጪ ወደ ሰው የሚገባ ነገር ሰውን ምንም እንደማያረክሰው አይገባችሁምን?
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።