La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ሄሮድስ፦ “የምትፈልጊውን ነገር ጠይቂኝ! እኔም እሰጥሻለሁ!” ሲል በመሐላ ቃል ገባላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምትለምነውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 14:7
6 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም “አስቴር ሆይ፥ ስለምን መጣሽ? ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የንጉሠ ነገሥት መንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” አላት።


የወይን ጠጅ በመጠጣት ላይ ሳሉም ንጉሡ አስቴርን “ማናቸውንም የምትፈልጊውን ነገር ጠይቂኝ፤ ይፈጸምልሻል፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ልሰጥሽ ዝግጁ ነኝ!” አላት።


የወይን ጠጅ በመጠጣትም ላይ ሳሉ ንጉሡ “አስቴር ሆይ! ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የፈለግሺውን ነገር ሁሉ እፈጽምልሻለሁ፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” ሲል እንደገና ጠየቃት።


ዐይኑን በሰው ላይ የሚጠቅስ ተንኰልን ያቀደ ነው፤ ከንፈሩንም የሚነክስ ወደ ክፋት የሚያመራ ነው።


የሄሮድስ ልደት በሚከበርበት ቀን የሄሮድያዳ ልጅ መጥታ በተጋባዦች መካከል እየጨፈረች ሄሮድስን አስደሰተች።


እርስዋም በእናቷ ተመክራ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን አሁኑኑ ስጠኝ!” አለችው።