በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ።
ማቴዎስ 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በፍርድ ቀን፥ ከእናንተ ይልቅ በጢሮስና በሲዶና ይኖሩ ለነበሩት ቅጣቱ ይቀልላቸዋል እላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ቅጣቱ ይቀልላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። |
በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ።
“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ አደጋ ለመጣል ተነሥቶአል፤ ራሳቸው እስኪመለጥና ትከሻቸው እስኪቈስል ወታደሮቹን ከባድ ሸክም እንዲሸከሙ አድርጎአቸዋል፤ ይሁን እንጂ ንጉሡም ሆነ ሠራዊቱ በዚህ ሁሉ ድካማቸው ምንም ያተረፉት ነገር የለም።
“እናንተ የጢሮስ፥ የሲዶናና የፍልስጥኤም አውራጃዎች ሕዝብ ሆይ፥ ምን እያደረጋችሁ ነው? እኔን ለመበቀል ይቃጣችኋልን? ይህ ከሆነ ሥራችሁ ወዲያው በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እንዲመለስ አደርጋለሁ።
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር!
ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።
በዚህ ዓለም እኛ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንደሚኖረው እንደ መሆኑ ፍቅራችን ፍጹም ቢሆን በፍርድ ቀን ያለ ፍርሀት በፊቱ ለመቅረብ ሙሉ መተማመን ይኖረናል።
ታናናሾችንና ታላላቆችን ሙታን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ የሕይወት መጽሐፍ የሆነ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ ሙታንም በመጻሕፍቱ ተጽፎ በተገኘው ሥራቸው መሠረት ፍርድ ተቀበሉ፤