La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መጥምቁ ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሳለ፥ የክርስቶስን ሥራ በመሰማቱ ሁለት ደቀ መዛሙርት ልኮ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ ክርስቶስ በማድረግ ላይ ያለውን ነገር በሰማ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ልኮ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሐንስ በእስር ቤት ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦

Ver Capítulo



ማቴዎስ 11:2
11 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎን ምርኮ እስከ መሲሕ ዐሥራ አራት ትውልድ ነው።


ሄሮድስ ዮሐንስን አስይዞ በወህኒ ቤት አሳስሮት ነበር፤ ይህንንም ያደረገው የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በነበረችው በሄሮዲያዳ ምክንያት ነው።


ኢየሱስ የዮሐንስን መታሰር በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ምድር ሄደ።


በዚያን ጊዜ፥ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “እኛና ፈሪሳውያን ዘወትር እንጾማለን፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።


ሄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮዲያዳን ስለአገባ ዮሐንስን በእርስዋ ምክንያት አስይዞ በወህኒ ቤት አስሮት ነበር።


የገሊላውን ገዢ ሄሮድስን ግን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን በማግባቱና ሌላም ብዙ ክፉ ነገር በማድረጉ ገሠጸው።


አንዳንድ ሰዎች “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል” እያሉ ያወሩ ስለ ነበረ የገሊላ አገረ ገዢ የነበረው ሄሮድስ ኢየሱስ ያደረገውን ሁሉ በመስማቱ ተደናገረ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከዮሐንስ ይበልጥ ብዙ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርግና እንደሚያጠምቅ ፈሪሳውያን ሰሙ፤